የዓለም የምግብ ዋጋ እየገሰገሰ መሆኑ ለድሃ አገሮች ሥጋት ሆኗል
በብርሃኑ ፈቃደ
የምዕራቡ ዓለም በተለይም አሜሪካ በታሪኳ ከባዱን የድርቅ አደጋ እያስተናገች መሆኗን ተከትሎ፣ ድሆችና ተመጽዋች አገሮች በምግብ ዋጋ ንረትና በአቅርቦት ማጥ ውስጥ ሊወድቁ እንደሚችሉ ሥጋቶች እየተስተጋቡ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ተቋማት የምግብ አቅርቦት፣ ዕርዳታና ሰብዓዊ ድጋፎች ሊቀንሱ እንደሚችሉ እያስጠነቀቁ ይገኛሉ፡፡