በኢትዮጵያ የምግብ እጥረትና መፍትሄው

በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማትና ጥበቃ አስተባባሪ አቶ አቶ ፈቃደ ወንድማገኝ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት እጥረት ስላለ ሃገሪቱ ከውጭ ስንዴ ታስገባለች ። እንደ ሃላፊው ለስንዴ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረትና በአጠቃላይ የምግብ እጥረትን ለመከላከል መስሪያ ቤታቸው የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል ።