የወለኔ ፓርቲ አመራሮችን በመግደል የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በይበቃል ጌታሁን

መስከረም 11 ቀን 2005 ዓ.ም. ሁለት የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ወሕዴፓ) የወረዳ አመራር አባላትን በጥይት ገድለዋል የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡