የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የመጀመርያው ፈተና

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከትናንት በስቲያ ምሽት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ወደ አሜሪካ ከማቅናታቸው በፊት፣ ለሦስት ቀናት ያህል የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንቶችን ለማደራደር ከፍተኛ የማግባባት ሥራ ላይ ተጠምደው ነበር፡፡