የሙስሊሞች ተቃውሞና እስራት ቀጥሏል

በሞባይላቸው መልእክት የተላላኩ እየታደኑ ነው

Ethiopia Zare ቅዳሜ መስከረም 15 ቀን 2005 ዓ.ም. Sebtember 22, 2012)፦ የመለስ ዜናዊ ሞትና የቀብር ሥርዓታቸው አፈጻጸም ጉዳይ ረገብ አድርጎት የቆየው የሙስሊሞቹ የመብታችን ይከበር ጥያቄ ዓርብ መስከረም 11 ቀን 2005 ዓ፣ም በታላቁ አንዋር መስጂድ ሲቀጥል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሙስሊሞች “መሪዎቻችን ይፈቱ! ያታሰሩት ሳይፈቱ የዑላማዎች ምርጫ አይካሄድም! ምርጫው የሚካሄደውም በመስጂድ ብቻ መሆን አለበት!መንግሥት ከጣልቃ ገብነት ተግባሩ ያታቀብ!…” የሚሉና ሌሎች የመብት ማስከበሪያ ጥያቄ ድምፆችን “አላህ ወ አክበር!” ከሚለው ተክቢራ ጋር ደጋግመው አሰምተዋል፡፡