የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱዓለም አራጌ ንብረት ታገደ

በታምሩ ጽጌ

በሽብር ወንጀል በተመሠረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ተብለው 18 ዓመታት የተፈረደበትጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ እድሜ ልክ የተፈረደበት የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አንዱዓለም አራጌና  በሌለበት 15 ዓመታት የተፈረደበት አበበ በለው፣ ንብረት ላይ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡