አይኤምኤፍ በዓባይ ግድብ ላይ የወጣው ዘገባ የተሳሳተ ነው አለ

በጋዜጣው ሪፖርተር

ባለፈው ሳምንት የቡሉምበርግ የዜና አውታር የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የዓባይ ግድብ ግንባታ እንዲቀዛቀዝ የኢትዮጵያ መንግሥትን አሳሰበ በሚል ያሰራጨው ዘገባ የተሳሳተ ነው ሲል አይኤምኤፍ አስተባበለ፡፡