የሃይለማርያም አንገት

ሃይለማርያም ደሳለኝ Hailemariam Desalegneተስፋዬ ገብረአብ

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዚዳንት ሆነው በተመረጡ ጊዜ በመከላከያና በሲቪል የህወሃት አባላት ዘንድ አቧራው ጨሶ እንደነበር አስታውሳለሁ። አባላቱ የፖለቲካውን ጨዋታ አልተረዱትም ነበር። በወቅቱ የነጋሶ ሹመት የይስሙላ መሆኑን ማስረዳት፣ ለህወሃት መሪዎች ፈተና ሆኖባቸው ነበር። ህወሃት አሁንም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞታል። ምናልባትም በቀጣዩ የሃይል አሰላለፍ የህወሃት የበላይነት እንደተጠበቀ መሆኑን ማሳመን ካልቻሉ መፈንቅለ መንግስት ሊያጋጥም ይችላል።