“መለስ ስለሞቱ የስዬ ጎራዴ ወደ አፎቱ”

አዜብ ጌታቸው

አቶ ስዬ አብርሃ በአቶ መለስ የቦናፓርቲዝም ስሌትና ማጣፋት ህይወታቸውን ለመስጠት ከቆሙለት ድርጅት መባረራቸው ሳይበቃ 6 ዓመታትን በዘብጥያ አሳልፈዋል፡፡ በኔ እምነት የአቶ መለስ አይራሬነትና ጭካኔ ከተገለጠባቸው በርካታ ውሳኔና እርምጃዎቻቸው አንዱና ዋንኛው ይህ በአብሮ አደግ ጓደኞቻቸው ላይ የወሰዱት ምህረት የለሽ እርምጃ ነው።