ወታደራዊ ሚስጥሮችን ለኦነግና ለኤርትራ አሳልፎ በመስጠት የተጠረጠሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተከሰሱ

–    አገርን አደጋ ላይ የሚጥል ሚስጥር አሳልፈው መስጠታቸው ተጠቁሟል

በታምሩ ጽጌ

በሚስጥር የሚጠበቁና በሕዝብ በይፋ የማይታወቁ ወታደራዊ ሚስጥሮችን ለኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) እና ለኤርትራ የደኅንነት ሠራተኞች አሳልፈው ሰጥተዋል በሚል የተጠረጠሩ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ሁለት ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡