ፕሬዚደንት ኦባማን ለድጋሜ ምርጫ ለምን አንደምደግፋቸው
ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)
በ2008 ምርጫ ወቅት ዕጩውን ፕሬዜዳንት ኦባማን በደስታ ነበር የደገፍኳቸው? በእርግጠኝነት! ባለፉት አራት ዓመታት ጊዜ ያከናወኑት ሁሉም ተግባራቸውንስ የምስማማበት ነው? ፈጽሞ! በ2008 የገቡትን ቃላቸውንስ በሙሉ አክብረዋል? እንዲያዉም! በ2012 በፕሬዜዳንት ኦባማ ቅር ተሰኝቻለሁ? በሚገባ! ግን: እኮ አኔ ብቻ ሳይሆን በ2008 የደገፏቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካኖችም ቅሬታ አላቸው፡፡