እንደ አንድ ሕዝብ እንዳለቀስን እንደ አንድ ሕዝብ እንገስግስ!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ታመሙ መባሉን እንደሰማ ለሁለት ወራት አዝኖና ደንግጦ፣ አረፉ መባሉን ከሰማ ወዲህም ለሁለት ሳምንት ሙሉ በመሪር ሐዘን በመዋጥ አልቅሶና ተላቅሶ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትሩን አፍሪካና ዓለም በተገኙበት ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት ፈጽሞ ተሰናብቷል፡፡ እጅ እንነሳለን እንዳሉት እኛም እጅ እንነሳለን ብሎ፡፡