ተቃዋሚዎች መነጋገር ይፈልጋሉ
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሕልፈት ተከትሎ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች መግለጫዎች እየወጡ ነው፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግሥት ሽብርተኞችና ከሃዲዎች እያለ የሚጠራቸው ሁለት ተቃዋሚ ድርጅቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕልፈት በኋላም የሚፈልጉት ከመንግሥቱ ጋር ወመያየት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በየድርጅቶቻቸው ስም መግለጫዎቻቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ያሳወቁት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ወንድምአገኘሁ ደነቀ፣ የአረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አሥራት እና የኦሮሞ የምክክር መድረክ የውጭ ጉዳይ ተጠያቂና ቃልአቀባይ አቶ ሌንጮ ባቲ ናቸው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከመለስ ጋር የግል ፀብም ሆነ ቂም እንደሌላቸው ያመለከቱትና ክፉም …