ውይይት፥ ድህረ መለስ ኢትዮጵያ፤ አማራጮችና ፈተናዎች

ለሳምንታት ሲያነጋግርና የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ስቦ ከቆየው የጤናቸው ሁኔታ በኋላ እስካሁን ይፋ ካልተደረገው ሕመማቸው በማገገም ላይ ሳሉ በገጠማቸው ኢንፌክሽን ሣቢያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይፋ የተደረገው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አስተዳደር ተተኪ ዕጣና የሚኖረው ገጽታ ምን ሊመስልና ሊሆን ይገባዋል?» የሚለውም እንዲሁ በአንጻሩ እያነጋገረ ነው።

ከ99 በመቶ በላይ የአገሪቱን ፓርላማ የሚቆጣጠረው ፓርቲ ከመሪው ሞት በኋላ ምን ዓይነት ገንቢ የተሃድሶ ለውጦችን ያካሂድ ይሆን? የቱን ያህልስ አሳታፊ ይሆን? ወቅታዊ ሁኔታዎች፥ አማራጮችና የአዲሱ መንግስት ፈተናዎች? በዝርዝር የሚዳሰሱበት ተከታታይ ውይይት ነው።

ድህረ መለስ ኢትዮጵያ።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራም የሕብረተሰብ …