የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ክሱ ተቋርጦ ተለቀቀ
• ለሁለት ቀናት በጨለማ ቤት ውስጥ ታስሬያለሁ አለከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕመም ጋር በተያያዘ ዘገባ ምክንያት የሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ሕትመቱ እንዳይሰራጭ የታገደውና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት “አላትም ብሏል” በሚል መታተም ያቋረጠው የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ዋስትና ተከልክሎ ከታሰረ ከስድስት ቀናት ቆይታ በኋላ ነሐሴ 22 ቀን 2004 ዓ.ም. ክሱ ተቋርጦ ከእስር ተፈታ፡፡