አድናቆት ምስጋናና ክብር ወርቅ ለሆነው ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

ወርቅ በእሳት ይፈተናል፡፡ በእሳት የሚፈተነው ግን የወርቅ ማዕድን ብቻ አይደለም፡፡ ወርቅ ሕዝብ ጭምር እንጂ፡፡ ወርቅ ሕዝብ፣ ጨዋ ሕዝብ፣ አስተዋይ ሕዝብ፣ ቅንና አገር ወዳድ ሕዝብ በችግርና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ይፈተናል፡፡