የአቶ መለስ ሕልፈት በኅብረተሰቡ የፈጠረው ድባብ

ባለፈው ማክሰኞ ማለዳ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ዜና ዕረፍት እንደተሰማ ኢትዮጵያ በዕንባ ተጠመቀች፡፡ ከማክሰኞ ማለዳ አንስቶ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ሐዘኑ በዋና ዋና ከተሞችም ሆነ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በርትቶ ቀጥሏል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜና ዕረፍት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካና በመላው ዓለም ናኝቷል፡፡