ፓርላማው አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
በዕረፍት ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለነገ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሕልፈተ ሕይወት ተከትሎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡ ሆኖም ምክር ቤት አሁን የጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የአቶ ኃይለ ማርያምን ሥልጣን በይፋ ለማፅደቅ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡