የፓርላማው አስቸኳይ ስብሰባ ተራዘመ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ጠርቶት የነበረው አስቸኳይ ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ፡፡
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ አስቸኳይ ስብሰባው ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመው የአቡነ ጳውሎስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ስለሚፈጸም ነው፡፡ ምክር ቤቱ ጠርቶት በነበረው አስቸኳይ ስብሰባ የአገሪቱ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ሥልጣን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡