የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀብር ሥነ ሥርዓት ነሐሴ 27 ቀን ይፈጸማል
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም. እንዲፈጸም መንግሥት አስታወቀ፡፡ ባለፈው ሰኞ ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከማክሰኞ ጀምሮ ብሔራዊ የሐዘን ቀን በመላ አገሪቱ ታውጇል፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን የሚያስፈጽም ሰባት አባላት ያሉት ብሔራዊ ኮሚቴም ተቋቁሟል፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን አስመልክቶ ዝርዝር መግለጫ አልተሰጠም፡፡