መለስ ዜናዊ 1947-2004

ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት የመሯት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባጋጠማቸው ድንገተኛ የኢንፌክሽን ሕመም ሰኞ ሌሊት 5፡40 ላይ ሕይወታቸው ማለፉን መንግሥት ካስታወቀ በኋላ፣ ትናንት ምሽት ላይ አስከሬናቸው ከብራሰልስ ሴንት ሉክ ሆስፒታል አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አስከሬን በርካታ የመንግሥት ባለሥልጣናት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ሲቀበሉና፣ በርካታ ዜጎችም ከአውሮፕላን ማረፊያ እስከ ታላቁ ቤተ መንግሥት አቀባባል አድርገውለታል፡፡