ሕዝብ ታላቅነትን መንግሥት በሳልነትን ያሳዩ!

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አረፉ የሚለውን ዜና የሰማ ሀቀኛ ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ ድንጋጤም ሐዘንም ተሰምቶታል፡፡ እኛም፡፡ ችግር ቢኖርም፣ ጉድለት ቢኖርም፣ እንደ ፖለቲካ ድርጅት መሪና እንደ አገር መሪ ታሪክ ለዘለዓለም በኩራት የሚያስታውሳቸው በርካታ አኩሪ ሥራዎችን ሠርተዋልና፡፡ ለአፍሪካም ጭምር፡፡