የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ አስከሬን ከሀገር ውጭ ነው

  • “ቤተሰቦቻቸው አብረዋቸው ናቸው”
  • “ቀብራቸው እስኪፈፀም ብሔራዊ የኀዘን ቀን ታውጇል”
  • “ፓርላማው በቅርቡ ተሰብስቦ ም/ጠ/ሚኒስትሩን ቃለ-መኃላ ያስፈጽማቸዋል” አቶ በረከት ስምዖን

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ለመጨረሻ ጊዜ ለህዝብ የታዩበት PM Meles Zenawis’ last public appearance

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነኀሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም. August 21, 2012)፦ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን በዜናውቸው ዛሬ ጠዋት ላይ የጠ/ሚ መለስ ዜናዊን ማረፍ ከዘገቡ በኋላ በአንዳንዶች ላይ መደናገጥን፣ በአንዳንዶች ላይ ኀዘን የተስተዋለ ሲሆን፤ ታክሲ ላይ ሲያለቅሱ የታዩ ጥቂት ሰዎችም ነበሩ። አብዛኛው ሰው የመለስን መሞት ተለማምዶት ከመቆየቱ የተነሳ የአብዛኛው ሰው ዝምታ እንደመለስ ያለ አነጋጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሞቱን ዜና የሰማ አይመስልም። ሁሉም ሰው የተለመደ ሥራውን እና የተለመደ እንቅስቃሴውን ቀጥሎ ተስተውሏል።