በአንዋር መስጊድ ረብሻ አስነስተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው

የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባንና በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ክብር የሚሰጠውን 1433ኛውን የረመዳን ወር ፆም ተከትሎ በተነሱ ረብሻዎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ በርካታ ሰዎች፣ ነሐሴ 10 እና 11 ቀን 2004  ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው፡፡