ለግዙፉ የኢትዮ ቴሌኮም ፕሮጀክት የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ምላሽ ዘግይቷል
ኢትዮ ቴሌኮም በቢሊዮን ዶላሮች ሊያካሂደው ለተዘጋጀበት ግዙፍ የቴሌኮም መሠረት ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዜድቲኢና ህዋዌ የተባሉት ሁለት የቻይና ኩባንያዎች የተፋጠጡ ሲሆን፣ የሁለቱ ኩባንያዎች ቴክኒካዊና ፋይናንሻል ፕሮፖዛሎች ግምገማ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እንዲያፀድቀው ቢላክም፣ ምላሽ እንዳልተሰጠበት ለፕሮጀክቱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡