ብቃት የሌላቸው ተሽርካሪዎች በሕገወጥ መንገድ ቦሎ እየተሰጣቸው መሆኑ ተጠቆመ

•    የቴክኒክ ምርመራው ሒደት የተሽከርካሪ አደጋውን ያባብሰዋል የሚል ስጋት ፈጥሯል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት ባለሥልጣን በየዓመቱ በተሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገውን የቴክኒክ ምርመራ እያከናወነ ቢሆንም፣ ብቃት የሌላቸውና ከአገልግሎት ውጭ  መሆን ለሚገባቸው ተሽከርካሪዎች፣ በሕገወጥ መንገድ የቴክኒክ ምርመራውን በብቃት አልፈዋል በማለት ቦሎ እየተሰጣቸው መሆኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡