ረሃብ ለሚፈትናት አፍሪካ ኦሊምፒክ አዲስ ተስፋ ሆኗል

የአምናው የምሥራቅ አፍሪካ ድርቅና ረሃብ ትቶት ያለፈው ሰቆቃ አሁንም ድረስ የሚታወስ ሲሆን፣ በአፍሪካ ቀንድ 16 ሚሊዮን ሕዝብን ለረሃብ ያጋለጠው የአምናው የምግብ እጦት ጉዳይ ዘንድሮም 10 ሚሊዮኖችን ምጽዋት ጠባቂ አድርጎ እንደሚገኝ የዓለም ባንክ አመልክቷል፡፡