“ሆያ ሆዬ… ያች ድንክ አልጋ… ሆ… አመለኛ” (ሊያነቡት የሚገባ)
ተመስገን ደሳለኝ – አዲስ አበባ
በልጅነት ዕድሜያችን ከሚወደዱ እና ከሚናፋቁ ወራቶች ነሐሴ ዋነኛው ነው። በተለይ ለብላቴናዎች። ለወሩ ተወዳጅነት ምክንያት የሆነው ደግሞ በ‹‹ሆያ ሆዬ›› ጭፈራ የሚከበረው የ‹‹ቡሄ›› ባህል በዚህ ወር መሆኑ ነው። ስለዚህም ከወሩ የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ‹‹ጅራፍ›› እየገመዱ በሚያስጮኹ ማቲዎች መንደሮች ይታመሳሉ። በዚህ አይነት መልኩ እየተዝናኑ ይቆዩና ዕለቱ ሲደርስ ተቧድነው ‹‹ሆያ ሆዬ›› ዕያሉ በየቤቱ ይዞራሉ።