የውጭ ጉዳይ ዜናዎች

በሙሉነህ ዮሃንስና የውጭ ጉዳይ ምንጮች የተጠናከረ (ጁላይ 31 2012)

  • አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስን ሲያስታምም ከርሞ ከብራስልስ ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ ነው!
  • አምባሳደር ሙሉጌታ አለምሰገድ ባጣዳፊ ቤተሰቡን ወደ ጣሊያን አሸሸ!
  • አሜሪካን ሃገር በአምባሳደርነት ማእረግ ያሉ አራት ዲፕሎማቶች ከአበበ ገላው ጋር በተያያዘ ጠቅልለው እንዲመለሱ ታዘዙ!
  • መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብና የባለስልጣናት ቤተሰቦች ወደ ኬንያ እየተሸጋገሩ ነው!

አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ

ህወሃት በጫካ እያለ ጀምሮ የድርጅቱን ገንዘብ ውጭ ሃገር በማንቀሳቀስ የሚታወቀውና በአሁኑ ወቅት በምክትል ሚኒስትርንት ስም ውጭ ጉዳይን የሚያዘው ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስ ዜናዊ ከታመመ ጀምሮ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ሄድ ኦፊስ) አካባቢ ጠፍቶ መክረሙን በቦታው ያሉ ሰራተኞች አረጋግጠዋል።