ኢትዮ ቻናል ጋዜጣና ሳምሶን አድቨርቲይዚንግ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘጉ

–    አቶ ሳምሶን ማሞና ባለቤቱ ታስረው በ200 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ

በሳምንት ሁለት ቀን (ረቡዕና ቅዳሜ) ለተወሰነ ጊዜ እየታተመ ከተሰራጨ በኋላ፣ በሕትመት ዋጋ መናር ምክንያት በሳምንት አንድ ጊዜ (ቅዳሜ) በመታተምና በመሰራጨት ላለፉት አምስት ዓመታት የቆየው ኢትዮ ቻናል ጋዜጣና ለ15 ዓመታት የማስታወቂያ ሥራ ሲሠራ የቆየው ሳምሶን አድቨርታይዚንግ፣ ከትናንት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጉ መወሰኑን ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡