የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ስትራቴጂክ ከሚባሉት ውጪ 20 የልማት ድርጅቶችን ሊሸጥ ነው

የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ስትራቴጂክ የሚላቸውን በማስቀረት፣ የተቀሩትን 20 የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በተያዘው የበጀት ዓመት ወደ ግል ለማዘዋወር አቀደ፡፡