ፀረ ሙስና ኮሚሽን የመንግሥት የግዥ መመርያን ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው
– ‹‹ደፋር ለመባል ሚኒስትር እንከሳለን ብለን ዕቅድ አንይዝም›› ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን
በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ሙስና ከሚፈጸምባቸው የሥራ መስኮች በዋናነት የሚጠቀሰው የኮንስትራክሽን ዘርፉ መሆኑን በመጠቆም፣ አሁን እየተሠራበት የሚገኘውን የመንግሥት የግዥ ሥርዓት መመርያን ለመለወጥና ቁጥጥሩን ለማጠናከር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡