የሶርያ መንግሥት ከባለሥልጣናቱ የገጠመው ችግር
የሶርያ ጠቅላይ ሚንስትር ሪዣድ ሂጃብ የፕሬዚደንት በሻር አል አሳድ መንግሥት በራሱ ሕዝብ ላይ ያካሂደዋል ያሉትን የጀምላ ጭፍጨፋ በመቃወም በትናንቱ ዕለት ከድተው የተቃዋሚውን ጎራ መቀላቀላቸው የሚታወስ ነው። የሶርያ መንግሥት ግን ሂጃብ ከሥልጣናቸው እንደተባረሩ ነው ያስታወቀው።
ውጭ የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደሚሉት፡ የሶርያ ጠቅላይ ሚንስትር እና በሶርያ የተቃዋሚው ወገን ቃል አቀባይ ዘገባ መሠረት፡ ሁለት የመንግሥት ሚንስትሮች እና ሦስት ከፍተኛ የጦር ኃይሉ መኮንኖችም የከዱበት ድርጊት የፕሬዚደንት አሳድ መንግሥት ከውስጥ በገጠመው ተቃውሞ እየፈራረሰ መሆኑን ጠቋሚ ነው።
ይህ በዚህ እንዳለ፣ የሶርያ ፕሬዝደንት በሽር አልአሰድ ላለፉት 17 ወራት የተነሳባቸዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ ለመጨፍለቅ ቆርጠዉ መነሳታቸዉን አመለከቱ። ከሁለት ሳምንታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ያሉት አልአሰድ፤ የሶርያ ህዝብና መንግስት የአሸባሪዎችን ሀገርና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት መዘጋጀታቸዉን መግለፃቸዉን ሮይተርስ የሀገሪቱን የዜና ወኪል በመጥቀስ ዘግቧል። አልአሰድ ስለጤና ማጣታቸዉም ሆነ ስለመገደላቸዉ ሲናፈስ የነበረዉን ወሬ ለጉብኝት ደማስቆ ከሚገኙት የኢራን የከፍተኛ ብሄራዊ የደህነት ምክር ቤት ኃላፊ ሳኢድ ጃሊሊ ጋ በመሆን በቴሌቪዥን ብቅ በማለትም መሠረተ ቢስ እንደሆነ አሳይተዋል። ያዳምጡ