የውጭ ኢንቨስተሮች በአደንዛዥ ዕፅ ንግድ ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው

ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች  የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ፣ አደንዛዥ ዕፅ በማምረት፣ በማዘጋጀትና ወደ ተለያዩ የዓለም አገሮች ሲልኩ ነበር የተባሉ የጃማይካና የኔዘርላንድ ዜጎች፣ ከኢትዮጵያውያን ተባባሪዎቻቸው ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዘው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡