ልጁን አስገድዶ ለሦስት ዓመታት የደፈረው አባት በፅኑ እስራት ተቀጣ

–    በሥነ ልቦናዋ ላይ ከባድ ጉዳት እንዳደረሰባት ተናግራለች

ነዋሪነቱ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 10/11 ውስጥ ነዋሪ የሆነው ሙሉጌታ ውብሸት የተባለው ግለሰብ ልጁን አስገድዶ በመድፈርና ለሦስት ዓመታት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈጽምባት መቆየቱ፣ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ በ18 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡