ፍራንስ ቴሌኮም ላቀረበው የኮንትራት ማራዘሚያ ጥያቄ መንግሥት ዝምታ መርጧል

–    አሥር የፍራንስ ቴሌኮም ከፍተኛ ባለሙያዎች በኢትዮጵያውያን ተተክተዋል

ፍራንስ ቴሌኮም ኢትዮ ቴሌኮምን ለማስተዳደር የኮንትራት ጊዜው እያበቃ በመሆኑ፣ ተጨማሪ የሁለት ዓመት ጊዜ እንዲራዘምለት ጥያቄ ማቅረቡ ቢሰማም መንግሥት ምላሽ አልሰጠም፡፡