የቁጠባ ቤቶች ግንባታ እንደሚጀመር ተበሰረ

መስከረም 2003 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በተካሄደው የኢሕአዴግ ስምንተኛው ጉባዔ የመኖርያ ቤቶችን እጥረት ለመቅረፍ በመላ አገሪቱ እንዲካሄድ የወሰነው የቁጠባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት፣ ከሁለት ዓመታት ‹‹ዝግጅት›› በኋላ ባለፈው ሐሙስ በይፋ መጀመሩ ተበሰረ፡፡