ሰበር ዜና፡ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዕረፍት ላይ መሆናቸውን ገለጸ

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ  በዕረፍት ላይ መሆናቸውን ገለጸ፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያገጠማቸውን ቀላል የጤንነት ችግር ታክመው በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡