የታሪክ ዘይቤ (ብዕለ ስብሐትሁ ወጥበቢሁ!)

ሰሎሞን ተሠማ ጂ.

በመጀመሪያ፣ አንድ ሰው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመጓዝ ላይ ሳለ፣ በአጋጣሚ አንድ ወርቃማ-ቁልፍ ቢጥል በዚያው መንገድ እንደሚመለስ አያጠራጥርም። ሰውዬው የጠፋበትን ቁልፍ ለማንሳት የፈለገውን ያህል ጊዜ (ዘመን) ቢቆይም እንኳ፣ ቁልፉን ፍለጋ በዚያው በተጓዘበት መንገድ ይመለሳል። እንጂ በሌላ አቋራጭ-መንገድ አይሄድም።