ህወሓት እና የመስዋዕትነት ወጥመድ
ያሬድ አይቼህ
የደርግን ወታደራዊ መንግስት ለማስወገድ በተደረገው ትግል የብዙዎች ህይወት ተሰውቷል። ከቀይ ሽብር ጀምሮ ኢህአዴግ አዲስ አበባን እስከተቆጣጠረበት ቀን ድረስ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የህይወት፣ የአካል፣ የንብረት፣ የእድሜና የስነልቦና መስዋዕትነት ከፍለዋል። ሆኖም ግን መስዋዕትነት መክፈል አንድ ጊዜ ሆኖ የሚያልፍ ክስተት አይደለም – መዘዝም አለው።