የሸካ ሽማግሌዎች ኃይሌ ገብረሥላሴ ደን እንዳይጨፈጭፍ ገዘቱት

ዝነኛው አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በግብርና ሚኒስቴር አማካይነት በሊዝ የተፈቀደለትን 1,500 ሔክታር መሬት ለመረከብ በደቡብ ክልል ሸካ ዞን በተገኘበት ወቅት፣ የአካባቢው ሽማግሌዎች በመሬቱ ላይ ያለውን ደን እንዳይጨፈጭፍ ገዘቱት፡፡