‹‹ይቅርታ›› የኢህአዴግ ቃጭል? ወይስ…

በተመስገን ደሳለኝ (ፍትህ ጋዜጣ – አዲስ አበባ)

አዲስ አበባ በለውጥ ፍላጐት ከአፍ እስከ ገደቧ ታጥናለች። እዚህም እዚያም የፖለቲካ ወግ ይጠሰቃል። በቡድን ሆነው፣ በስሜት ተውጠው በፖለቲካ ጉዳይ የሚከራከሩ በርክትዋል፡ ፡ ለዓመታት የፖለቲካ ጉዳይ ‹‹ፆም›› የሆነባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሳይቀሩ ጎራ ለይተው በሚከራከሩ ሠራተኞቻቸው ተፈስገዋል፡፡ ‹‹ቅንጅቱ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል ድምፅ አግኝቷል›› ይላል አንዱ። ‹‹ቢሆንም ኢህአዴግ ይገግማል!›› ሲል ይመልሳል፤ ኢህአዴግ በምርጫ ስልጣን አይለቅም የሚል አቋም ያለው ተከራካሪ፡፡