የዕቃ አስተላላፊዎች ማኅበር ዕቃዎችን የማጓጓዝ ሥራ በሞኖፖል ሊያዝ አይገባውም አለ

•    ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቤቱታ አቀረበ

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ዕቃ የማጓጓዝ ሥራዎች በሙሉ በሞኖፖል ተቆጣጠሮ ከሥራ ውጭ አድርጎናል ያሉ የዕቃ አስተላላፊ ኩባንያዎች፣ በማኅበራቸው አማካይነት አቤቱታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቀረቡ፡፡