የአንዱዓለም አራጌ የቅጣት ማቅለያ አቀራረብ የችሎቱን ሐሳብ አስቀየረ
በተከሰሱበት የሽብርተኝነት ወንጀል ጥፋተኛ መሆናቸው ተረጋግጦ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ፣ የቅጣት ማቅለያ ሐሳብቸውን እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ሲያሳውቅ በቅድሚያ ሐሳባቸውን ያሰሙት አቶ አንዱዓለም አራጌ ቢሆኑም፣ አቀራረባቸው ቅጣቱን በሚያቀልላቸውና ሕጉን በተከተለ መልኩ አይደለም በሚል ችሎቱ ሐሳቡን ቀይሮ፣ ሁሉም ተከሳሾች የቅጣት ማቅለያ ሐሳብቸውን በጽሕፈት ቤት በኩል በጽሑፍ እንዲያቀርቡ አዘዘ፡፡