አምስት የኢትዮጵያ ጠላቶች


‹‹ኢትዮጵያ አገሬ›› ከሚለው ሐረግ በቀር በዚህ ዘመን አንገት የሚያስቀና ነገር ማግኘት እየከበደ ነው፡፡ እሴቶቻችን እየተሸረሸሩ፣ ፍቅራችን እየጠወለገ፣ ተስፋችን እየመነመነ.. መጥቷል፡፡ መንስኤው እንደውጤቱ እልፍ ነው፡፡ እኔም እንደወትሮዬ አምስት አጀንዳዎችን አንስቼ አንድነታቸውን የማስደመድምበት ምክረ መጣጥፍ ይዤ ቀርቤያለሁ - እነሆ!

1ኛ
‹‹ገበታ ንጉሥ ነው››
ገበታ እንደንጉሥ የሚቆጠርባት ኢትዮጵያ ገበታን ለማግነን ምክንያት አላት፡፡ የዓለም ስልጣኔ እምብርት የሆነችው ግብጽ ጥንታዊና ዘመናዊ ከተሞቿ የተቆረቆሩት በአባይ ወንዝ ዳርቻ ነው፡፡ ግብጽ ምድሯ ውሃ ባያፈልቅም ከደጇ በሚያልፈው ውሃ ሕዝቦቿን ከረሃብ ለመታደግ ችላለች፡፡ ‹‹ከሞኝ ደጃፍ ምሳር ይቆረጣል›› ነውና ተረቱ ኢትዮጵያ ግን የረሃብ ምሳሌ ነች፡፡ ከሰማይ ዝናብ ዘነበ/አልዘነበ በሚል የምግብ ዋስትናዋን በሚትዮሮሎጂ ዕድል ላይ የጣለችው ኢትዮጵያ የረሃብን ነገር ታውቀዋለች እና ‹‹ገበታ ንጉሥ ነው›› እያለች ብትተርት አይፈረድባትም - ረሃብ አንደኛ ጠላቷ ነውና፡፡

2ኛ
‹‹ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም››
ኢትዮጵያውያን አማኞች ናቸው፡፡ ክርስትና ከመፈጠሩ በፊት አክሱም ሃውልትን ያስቆማቸው እምነታቸው ነው፡፡ ነገሮች ሁሉ በፈጣሪ ፈቃድ እንጂ በሰው ጉልበት ይሆናል ብለው አያምኑም፡፡ ይህንን በርካታ ምሳሌና የኑሮ ዘይቤያቸው ይመሰክራል፡፡ እርግጥ በዘመናዊዋ እና በቀድሞዋ ኢትዮጵያ መካከል ልዩነት ይኖራል ብሎ መጠርጠር መልካም ነው፡፡ እንደምሳሌም ጥንታዊዎቹ የአክሱም ሐውልትን ያቆሙት በትግል እንጂ በዕድል አይደለም፤ ሌላ ምሳሌ፣ ቀደምት የላሊበላ ታሪክ ጸሃፊዎች ላሊበላ የታነፀው እነዚህ ታሪክ ጸሃፊዎች የኢትዮጵያውያንን የእጅ ሥራ ‹‹ታድለው›› እንጂ ‹‹ታግለው›› ያገኙት ስላልመሰላቸው ከነዚያኞቹ እነዚህኞቹ ያንሳሉ - እምነትን በመምረጣቸው ብቻ ሳይሆን መታደልን ቁጭ ብለው በመጠበቃቸው፡፡

‹‹ጠንቋይ መቀለብ›› የተሰኘች አባባል አለች፤ ‹‹ማወቅን›› ትወክላለች፡፡ በአገራችን ‹አዋቂ› የሚለው ቃል ‹ጠንቋይ› ከሚለው እኩል ያገለግላል፡፡ የእጅ ሥራ ባለሙያዎች ጥሩ ስም የላቸውም - ‹‹ቡዳ›› ናቸው፡፡ አሁንም ድረስ በሥራው ግን በቶሎ የተሳካለት ሰው/ነጋዴ ‹‹ምን የተለየ ሥራ ሰርቶ ነው?›› ብሎ ሊማርበት ከሚፈልገው ይልቅ ‹‹አስጠንቁሎ/አስደግሞ ነው›› እያለ የሚያማው ተመልካች ይበዛል፡፡ ከሥራ ይልቅ ምትሃት ዋጋ አለው፡፡ ድህነቱንም ሮጦ ያመለጠ ሰው ግፋ ቢል ‹‹ፈጣሪ ረዳው›› ይባል እንደሆን እንጂ ‹‹ለፍቶ አገኘ›› የሚባልበት ጊዜ እምብዛም ነው፡፡ ኢትዮጵያ ችግር ላይ ነች - ዜጎቿ ለስኬት አቋራጭ መንገድ ያስሳሉ - አምልኮን ወይም እምነትን የሙጢኝ ብለው ‹‹የቆጡን ሲጠብቁ፣ የብብታቸው››ን ያጣሉ፡፡

3ኛ
‹‹ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ››
ኢትዮጵያውያን ንግሥና እና ሰማይን የምናነፃፅር ብቸኛ ዓለመኞች ነን፡፡ ንጉሥ ካ’ሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፈረዱ በቃ - አበቃ ብለን እጅና እግራችንን አጣጥፈን የምንቀመጥ ሰዎች ነን፣ ጭቆና ከንጉሥ ከመጣ አሜን ብሎ የሚሸከም ጫንቃ ያለን ፍጡሮች ነን - በልምድ፡፡ ይሄ ልምድ ከንጉሥ ጀምሮ እስከታችኛው እርከን ይወርዳል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን የሥራ ቦታ አለቆቻችን ሲሳሳቱ ደፍረን አናርማቸውም፣ ሲጨቁኑን አንታገላቸውም፣ መስመር ሲስቱ አንመልሳቸውም - ምክንያቱም ንጉሥ አይከሰስም፡፡ በዚህ መንገድ ብዙ አምባገነኖችን ፈጥረናል፣ ገና እንፈጥራለን - ንጉሥ ባለመክሰስ፡፡

4ኛ
‹‹ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል››
የጉበኝነት፣ ሙሰኝነት፣ በስልጣን መባለግ ወይም መበልፀግ በአገራችን ዕድሜው ስንት እንደሆነ ለማወቅ ይሄ ተረት መተረት የጀመረበትን ጊዜ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ሹመኞች ሊያገለግሉት የተሾሙለትን ሕዝብ መበዝበዝ እንደመብት ይቆጥሩታል፡፡ ጥንት ጀምሮ እስከዛሬ የዘለቀው የሹመኛ የመብላት ‹‹መብት›› ተሹሞ የማይበላውን፣ በተሾመበት መስክ ባይተዋር የሚያደርግ ነው፡፡ ተሹሞ ባለመብላቱ እንደሚቆጭ እየተነገረው አለመብላትን የሚመርጥ ምናልባትም ለሌሎች ሹመኞች ስለማይመች የሚወገድበት መንገድ ይመቻችለታል፤ ባልሰራው ወንጀል ይከሰሳል፣ የበይዎቹን ገፈት ይቀምሳል፡፡ ሹመኞች ሲበሉ የሚመለከቱ ሰዎች ‹‹ባለጊዜ›› ብለው ያልፏቸው እንደሆን እንጂ እንደወንጀለኛ አይሷቸውም፣ አይወቅሷቸውም፣ አያጋልጧቸውም፡፡ እንዲያውም ብዙዎቹን ሹመኞች የሚያባልጓቸው ሕዝቦች ናቸው፡፡ ለዚያ ነው ዛሬ፣ ዛሬ ብዙዎች ሹመትን የሚመኙት ለመብላት የሆነው - ሌላው ጠላታችን፡፡

5ኛ
‹‹እል’ፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል››
የተማረው፣ ያልተማረው፣ ድሃው፣ ሃብታሙ፣ ከተሜው፣ ገጠሬው - ሁሉም አንድ ሕልም አለው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጪ ወደ አንዱ አገር መኮብለል፡፡ እርግጥ ከላይ ተረቱ ‹‹ዛሬን ሲያልፉ ነገ እልፍ ይገኛል›› የሚል ትርጉም ሊሰጥ ይችላል፡፡ ይህም ቢሆን ችሎ ማሳለፍ፣ ‹ታግሎ› ሳይሆን ቅድም እንደታዘብነው ‹ታግሶ› ማሳለፍ ላይ ነው ዓላማው፡፡ ከዚያም በከፋ ግን ኢትዮጵያውያን አልፎ መሄድ እየተማርን ነው፡፡ ከ5 ዓሥርት ዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ የወጡ ሰዎች ስም ዝርዝር በጋዜጣ ይታተምባት የነበረችው አገር ዛሬ በፈላሾቿ (diasporas) ቁጥር አንድ አገር መመስረት የምትችል ሆናለች፡፡ ምክንያቱም ዜጎቿ ‹እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል› ብለው ያምናሉ፡፡ በዚህም አገራችን እልፍ የሚሰሩ ክንዶች፣ እልፍ የሚፈጥሩ ጭንቅላቶችን አጥታለች - ስደት ጠላቷን እየተከተለች፡፡

ድምር ውጤቱ?
ለጠላቶቻችን ማጣቀሻነት ተረትና ምሳሌዎቻችን የተጠቀምኩት ያለምክንያት አይደለም፡፡ ተረትና ምሳሌ የብዙዎች አስተሳሰብ ብዙዎችን በሚያግባባ መንገድ የሚገለፅበት ቋንቋዊ ዘይቤ ነው፡፡ እነዚህ ተረትና ምሳሌ ስር የሰደዱ ባሕልና አስተሳሰባችንን (mentality) ይነግሩናል፡፡ ሁሉም ታዲያ የምስራች የላቸውም - እዚህ እንደጠቀስኳቸው ያሉቱ መርዶ ናቸው፡፡ መርዶዎቻችንን ደምረን ስንመለከታቸው ድምራቸው አንድ ነው፡፡ ሁሉም የተዘረዘሩት የዕውቀት ማነስ ውጤቶች ናቸው፡፡ ይህንን መቅረፍ ደግሞ የሚቻለው በትምህርት ነው፡፡ ጥራት ያለው ትምህርትን ለሁሉም በማዳረስ፡፡

15 Comments on “አምስት የኢትዮጵያ ጠላቶች”

  1. But now Ethiopia is being destroyed by hodam elites but not uneducated Ethiopians. What has been going on in Ethiopia for the last 40 years was negative selective breeding. The killers remained while those who could have done something better for their country and people are killed.

  2. In Ethiopia we have bad schooling system,that is why we are in to all this
    If we unite and remove the little MAHFIA WEYANE,we can build a better Ethiopia and
    no one will make fun on us

  3. Ignorance is basically the root cause of our chronic problem. We must open the door and usher in the era of enlightenment, liberal education.

  4. I have no problem for the comments given to #2,3 and 4. But I believe the authoe is off mark on no.1 and 5.

  5. I think the number one enemy of Ethiopia is weyane. All are the result of dictatorship. Remove weyane and you will see a different picture of Ethiopia.

  6. በእርግጥ ቋንቋችንና አስተሳሰባችን በብዙ መልኩ መሻሻልና ከክፍለ ዘመኑ ጋር አብሮ መሄድ እንዳለበት እንደፀሀፊው ባምንም. የዋልድባን ገዳም የሚነካውን ፕሮጀክት እያንቀሳቀሱ ያሉት ኢንጂነሮች ናቸው ሂሮሺማ ላይ ከ 100000 እስከ 200000 ሲቪል የጨረሰ አቶሚክ ቦንብ የፈጠሩት አንቱ የተባሉ ሳይንቲስቶች ናቸው. የሰው ልጅ እንደኔ በሰላምና በፍቅር ለመኖር የሚጎሉት ግብረገብ ቅንነት መከባበር ወደ ባህሪው (ወደ ሰብአዊነት) መመለስ ሲሆን ነፃ የሆነች ኢትዮጲያን አባቶቻችን የደም መስዋዕትነት ከፍለው ሲያስረክቡን የቱኛውም ፕሮፌሰር መጥቶ ሳያስተምራቸው ነው

  7. Nice comment…Good analysis. We all need to learn from these Ethiopian proverbs and wake up to contribute something to our country. All of the points mentioned have strong messages and exposed us to examine ourselves.

  8. I do feel the ‘same as above `´Solomon`´, it is also our own society attitude to create a wrong interpretation towards a word splitting issues to make things complicated. Those saying were told long years back; so that it may be nothing at that time. Things get worst in evolutions of time and now we are at the worst level because we have got in decay systems of government structures.

  9. Few paragraphs but are chronic problems for over the 80 million peoples of Ethiopia
    I absolutely agree with the writer.

  10. What you mention in your poit(?)(1-5) is very known long time a go by most ethiopians. including your self. Now, the ethiopian people knows that the sourse of all mesasery is the tyranical government. and are also aware that this missery will continue as long as this gangester government exists.

    Finally, I would like to mention that, ” the great dam on Abay river” is a phoney schme plotted by the dictator him self to clinch in power. In your article one,

    ‹‹ገበታ ንጉሥ ነው››

    ገበታ እንደንጉሥ የሚቆጠርባት ኢትዮጵያ ገበታን ለማግነን ምክንያት አላት፡፡ የዓለም ስልጣኔ እምብርት የሆነችው ግብጽ ጥንታዊና ዘመናዊ ከተሞቿ የተቆረቆሩት በአባይ ወንዝ ዳርቻ ነው፡፡ ግብጽ ምድሯ ውሃ ባያፈልቅም ከደጇ በሚያልፈው ውሃ ሕዝቦቿን ከረሃብ ለመታደግ ችላለች፡፡ ‹‹ከሞኝ ደጃፍ ምሳር ይቆረጣል›› ነውና ተረቱ ኢትዮጵያ ግን የረሃብ ምሳሌ ነች፡፡ ከሰማይ ዝናብ ዘነበ/አልዘነበ በሚል የምግብ ዋስትናዋን በሚትዮሮሎጂ ዕድል ላይ የጣለችው ኢትዮጵያ የረሃብን ነገር ታውቀዋለች እና ‹‹ገበታ ንጉሥ ነው›› እያለች ብትተርት አይፈረድባትም – ረሃብ አንደኛ ጠላቷ ነውና፡፡

    if you want us to throw ower help to the dictator, the answer is clear and loude NO!

    We build our country on the grave of woyanee and ethno-fascist melese zenawi

  11. በሀሳቡ ላይ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ ነገር ግን
    በመፍትሔው ግን ትምህርት ብቻ ቢሆን ኖሮ
    እጅግ በጣም ብዙ ሙሁራን ለሆዳቸው ባላደሩ ነበር
    በኔ እምነት ቖራጥ ትግል የዚህ ችግር መቓጫ ነው እላለሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*