በነዳጅ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ ህዝብ እንዳያስቆጣ ወያኔ መለማመጥ ይዞአል

የዜረኛው ወያኔ አገዛዝ በነዳጅ ላያ ያደረገው ጭማሪ ህዝቡን ለአመጽ እንዳያነሳሳ በአስቸኳይ የዋጋ ማሻሻያ እንደሚያደርግ እና የዋጋ ንረቱን ለማረጋግት እየሠራ መሆኑን ነጋ ጠባ በፕሮፖጋንዳ ማሰራጫዎቹ የመገናኛ ብዙሃን እያስተላለፈ እንደሆነ ለማወቅ ተችሎአል።

ለህዝብ ካለው ንቀት የተነሳ እንዳሻው ህዝብን በመዝለፍ የሚታወቀው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ የተጠራቀመ የህዝብ ብሶት ገንፍሎ መውጣቱ እንደማይቀር ከሰሜን አፍሪካው ህዝባዊ አብዮት ልምድ እየቀሰመ በመምጣቱ እስከ ዛሬ በነበረው የ20 አመት አገዛዝ ታይቶ የማይታወቅ ህዝባዊ ወገንተኛነት ለማሳየት ደፋ ቀና እያለ እንደሚገኝ ለሥር ዓቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለግንቦት 7 ዘጋቢ ገልጾዋል። ቀደም ሲል የወያኔ ፓርላማ ተሿሚዎች ታማኝነታቸውና ታዛዥነታቸው ለህወሃት ጌቶቻቸው ብቻ እንዳልነበረ ዛሬ ዛሬ ይወክላሉ ወደሚባሉባቸው የምርጫ ተብዬ ጣቢያዎች ድረስ ተጉዘው ህዝብ እንዲያነጋግሩና ችግራቸውን እንዲያዳምጡ ከመላክ ጀምሮ በሰበብ አስባቡ ያለ አግባብ ከሥራ የሚሰናበቱ የመንግሥት ሠራተኞችን ልብ ለማማለል ከአሁን ቦኋላ ማንም ሰው ከሥራ ላይ እንደማይቀነስ ፤ ደመወዝ ፤ እድገትና የነፃ ትምህረት ዕድል ለሁሉም እንደሚመቻች ባዶ ተስፋ  እየተገባ እንደሆን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከተለያየ ቦታ ያሰባሰባቸውን መረጃዎች ዋቢ በማድረግ ገልጾአል።

ወያኔ በተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲው የፈጠረውን የኑሮ ውድነት በነጋዴው ህብረተሰብ ላይ ለማላከክ ቸርቻሪ ነጋዴዎች ከወያኔ የጅምላ ንግድ ድርጅቶች በውድ ዋጋ የገዙትን የፍጆታ ዕቃዎች ከገዙበት ዋጋ በታች ቀንሰው እንዲሸጡ የዋጋ ተመን አውጥቶ የነበረ ሲሆን እነኚያ የዋጋ ተመን የታወጀባቸው የፍጆታ ዕቃዎች ከገቢያ ላይ ጨርሶ የጠፉ መሆናቸውን ዘጋቢያችን በላከልን ዜና አረጋግጦአል።