እየመረረ፣ እያመረረ፣ እያስመረረ…
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
ከኢትዮጵያ ሕዝብ ስንት በመቶው በራሱ ጉዳይ፣ በእህል በውሀው ጉዳይ ከማንሾካሾክ አልፎ አፍ አውጥቶ ይናገራል?፤ ለማንስ ይናገራል?፤ ማንስ ይሰማል?፤ በቴሌቪዥኑ፣ በራዲዮውኑ በጋዜጣዎች የሚነጋገረው በአጠቃላይ አምስት ሚልዮን ይሞላል? ሌላው ሰማንያ አምስቱ ሚልዮን ተመችቶት ነው? የዕለት እንጀራውን ማሳደድ ፋታ አልሰጥ ብሎት ነው? መነጋገሩን ንቆት ነው? ብሶቱን ለመናገር ዕድሉን ባለማግኘቱ ነው? ፈርቶ፣ ጎመን በጤና እያለ ነው?