በፍትህ ጋዜጣ ላይ የተጣለው አደጋ ስጋት ፈጥሯል

ፍትህ ጋዜጣ አልሻባብ ጋር ግንኙነት አለው የሚያስብል ኢሜል ተልኳል

(ሊያነቡትና ሊያውቁት የሚገባ)

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ተነባቢነት ያገኘችውና በህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ በአይነ ቁራኛ የምትጠበቀው የፍትህ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ባልደረቦችና በተለይም ሳምንታዊ ትችቶቹን በመጣጥፍ መልክ በማቅረብ የሚታወቀው ታዋቂው የፍትህ ጋዜጣ መስራችና ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ከፍተኛ ጫና የሚከቱ ማስፈራሪያዎች በመንግስታዊ ጋዜጦች ላይ እየወጡ መሆኑ ታወቀ። በተለይ ሰሞኑን ፍጹም በተለየ መልኩ ለተምስገን ዳሳለኝ መሰረት የለሽ ጽሁፎች በኢሜል እየደረሱት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።