መንግሥት ስካይፕና መሰል አገልግሎቶች አልተከለከሉም አለ
‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው – ኤርትራ የተሟላ ጦርነት መክፈት አትችልም››
አቶ ሽመልስ ከማል፣
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ
በቅርቡ በወጣው የቴሌኮሙኒኬሽን ረቂቅ አዋጅ የስካይፕና መሰል አገልግሎቶችን መጠቀም አለመከልከሉን መንግሥት አስታወቀ፡፡ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል ባለፈው ዓርብ ማለዳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ መንግሥት በኢንተርኔት አማካይነት የሚደረጉ ግንኙነቶችንና የስካይፕ አገልግሎት በሕግ አግዷል የሚባለው የተሳሳተ መረጃ ነው፡፡