አነጋጋሪው የዶክተር እሌኒ ገብረ መድኅን ስንብት

በዳዊት ታዬና በዘካሪያስ ስንታየሁ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ለመመሥረት ሐሳብ በማፍለቅና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የቆዩት ዶክተር እሌኒ ገብረ መድኅን፣ ኃላፊነታቸውን ለ38 ዓመቱ የባንክ ባለሙያ አቶ አንተነህ አሰፋ በማስረከብ ምርት ገበያን ሊሰናበቱ ነው፡፡